የተሻሻለ

የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ

ቤተሰብ የሕብረተሰብ የተፈጥሮ መነሻ በመሆኑና በሕብረተሰብና በመንግሥት ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ መሆኑን በማመን ፣ የመንግሥት ጥበቃ የሚገለጽበት አንዱ መንገድም የቤተሰብ ግንኙነትን በሕግ መደንገግና መግዛት መሆኑን በመገንዘብ፤

በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ አሁን ካለንበት የሕብረተሰብ የእድገት ደረጃ፡ በዋነኛነትም ከሕገመንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ማድረግ በማስፈለጉና ፡ በተለይም ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ መመሥረት ያለበት መሆኑንና በጋብቻ አፈፃፀም ፡ በጋብቻ ዘመንና በፍቺ ጊዜ የተጋቢዎችን የእኩልነት መብት የሚያስጠብቅ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ፤

የልጆችን ደህንነት ፣ አስተዳደግና አጠባበቅን አስመልክቶ ሕገ መንግሥቱና ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በሚጠይቁት መሠረት የሕፃናትን ደህንነት ቀደምትነት በሚሰጥ መልኩ ሕጉን አሻሽሎ መቅረጽ በማስፈለጉ፤

በቤተሰብ ውስጥ የሚነሱ ክርክሮችን ፍትሐዊ በሆነና በተቀላጠፈ ሁኔታ ብቃት ባለው አካል እንዲዳኙ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡ ይህን እውን ለማድረግም ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለፌደራሉ መንግሥት በሆኑ መስተዳድሮች ተፈፃሚነት የሚኖረው የቤተሰብ ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መውጣት ያለበት በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት ከዚህ የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 213/1992
ቀን: ሰኔ 27፥ 1992 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found