ለሦስተኛው የትምህርት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ ዩ·ኤ· 32 ሚሊዮን (ሠላሳ ሁለት ሚሊዮን ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢት ዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እኤአ ኖቬምበር 20 ቀን 1998 በአቢጃን የተፈረመ በመሆኑ ፤
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለምአቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆ ናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው ፣
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 2 ቀን 1991 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፤
በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ።