በአገልግሎት ላይ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም ዐቀፍ የልማት ማኅበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለከተሞች የአካባቢ አስተዳደር ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ 94 ሚሊዮን 700ሺ ኤስ.ዲ. አር (ዘጠና አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም ዐቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 15 ቀን 2011 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 726/2004
ቀን: ታኅሣሥ 12፥ 2004 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found