በአገልግሎት ላይ

የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ሥልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የሚወከሉበት የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደ አንድ ሕገ- መንግሥታዊ ተቋም የሕጎች ሁሉ የበላይ በሆነው በፌደራሉ ሕገ መንግሥት የተቋቋመ በመሆኑና ሥልጣንና ተግባሩ ጠቅለል ባለ መልክ በሕገ- መንግሥቱ ውስጥ የተመለከተ በመሆኑ፣

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተልዕኮውን በተሟላ መንገድ መፈጸሙ የሕገ መንግሥት የበላይነት፣ ሕገ- መንግስታዊነት፣ ዘላቂ ሰላም፣ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ ለማረጋገጥ፤ እንዲሁም አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ያለው አስተዋጽኦ የጎላ በመሆኑ፣

ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር ጋር በተያያዘ በጊዜ ሒደት በአፈጻጸም የታዩ የሕግና የአሰራር ክፍተቶችን መለየትና ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ፣

በጥቅል የተቀመጡት ኃላፊነቶችም ለአፈጻጸም ያመች ዘንድ በአዋጅ ዘርዘር ብለው እንዲደነገጉ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1261/2013
ቀን: ነሀሴ 13፥ 2013 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 519/1999

ሚያዝያ 16፥ 1999 ዓ.ም.
የተሻረ