ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ወይም አገልግሎቶቻቸውን በስፋት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በማስተዋወቅ የገበያ ማስፋፊያ ሥራ በመሥራት ውጤታማ መሆን እንዲያስችላቸው የፕሮሞሽን ውድድር ማካሄድ ስለሚፈልጉ፣
የሚያከሄዱት የፕሮሞሽን ውድድር ዓላማው ምርታቸው አገልግሎታቸው በስፋት ገበያ ውስጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ በመሆኑ በፕሮሞሽን ውድድሩ የሚሳተፈውን ህብረተሰብ መብት እንዲጠበቅ ማድረግና የመንግሥትንም ግዴታዎች በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል፣ የፕሮሞሽን ውድድር ማካሄድ ዓላማው ምርትን/አገልግሎትን ለህብረተሰብ ለማስተዋወቅ በመሆኑ፣
ጤናማ ያልሆነ ውድድር በድርጅቶች መሃል እንዳይፈጠር መከላከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ ድርሻ ኖሯቸው ተፈላጊ ውጤት ማለትም የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን ለመጠበቅና ለማበረታታት፣ አስተዳደሩ ከተቋቋመበት ደንብ ቁጥር 160/2001 እና በአስተዳደሩ በተካሄደው የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት ውጤት የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት እና በሥራውም ወቅቱ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ መመሪያ ቁጥር 42/2002 መሻሻል እንዳለበት በመታመኑ እና አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ማንኛውም ሰው ፈቃድ ሳይኖረው ማናቸውንም የሎተሪ ሥራ ማካሄድ አይችልም በሚል በመደንገጉ፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን ለማቋቋም በወጣው ደንበ ቁጥር 160/2001 አንቀጽ 21 መሠረት ይህን መመሪያ አሻሽሎ አውጥቶአል፡፡