የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባርለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/84 መሠረት የማታዳደር ሲሆን ዓላማወም በአዋጁ የተመለከቱትን ፡ –
- የትም/መሳሪያዎች ማምረት፣ ከሀገር ወስጥና ከወጪ አገር ገዝቶ ማቅረብ፣ የሥልጠናና የሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት፣
- ትርፋማትን ማሳደግና አስተማማኝ ገበያ መፍጠር እንዲሁም
- ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የማረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን ማካሄድ ነው።
ድርጅቱ የመንግሥት የልማት ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በትምህርት ዘርፍ ለተዘረጋው የዕድግትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትርጉም ያለው አስተዋጽዖ ለማበርከት የከርፖሬት ሥራ አመራር ሥርዓት ለማስፈን፣ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ለሜር፣ የባለድርሻ አካላትንና የመንግሥትን ጥቅምን በማስከበር የደንበኞችን ፍላጐት በላቀ ደረጃ ለማርካት ይሠራል፡፡
ድርጅቱ ይህንኑ ዓላማ ስኬታማ እንዲያደርግ በመምራትና በማስተባበር ስትራቴጂያዊ ሚናወን እንዲወጣ የአሠራር ሥርዓት በማዘርጋት የቅርብ ክትትል በማየደርግ የሥራ አመራር ቦርድ ይመራል።
የድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድና መሳካት ሆኖ ይህንኑ ወጥና ግልጽ በሆነ ደከም ያለ አፈፃፀም ሲታይ ለማረምና ይሆናል፡ ፡ ማኔጅመነት ትከረት በስትራቴጂክ ዕቅዱና በድርጅቱ ተልዕኰ መልኩ በመመዘን ወጠታና ትርፋማ ሆኖ እንዲገኝ ማበረታታት ተጠያቂነትን ለማስፈን የጭስችል አሠራር መዘርጋት ተገቢ ይሆናል።
ድርጅቱ ቀደም ሰል የሥራ አመራር ቦርድና የማኔጅመንት አባላትን ለማበረታታት በ2002ዓ.ም በቀድሞው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጅንሲ በተዘጋጀው መመሪያ መሠረት ሲሰራ የቆየ ሲሆን ይህም አሁን ካለበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተጠሪነት አኳያ ማስተካከል በማስፈለጉ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በ21/7/2010ዓ.ም በቁጥር1/1-8124/23296/35 በተፃፈ ደብዳቤ ማሻሻያ ተደርጐ እንዲቀርብ በሰጠው መመሪያ መሠረት
ተዘጋጅቷል፡፡
ስለሆነም ቀደም ሰል ለቦርድና ለሜ ጀመነት አባላት ይከፈል የነበረው ማበረታቻ ከተጣለባቸው ኃላፊነት አኳያ የማየነቃቃ ባለመሆኑ፣ የወቅቱን ሁኔታዎች ግምት ወስጥ ያላስገባ ሆኖ በማ ኘቱ የ ማ ምካ ማያው መስፈርት እና የክፍያው ሁኔታ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ በመሆኑም መመሪያው በ6 ክፍሎች የተዘጋጀ ሲሆን በከፍል 1 ጠቅላላ፣ በክፍል 2 የማበረታቻ ተግባር ኃላፊነት እና የወጠት መመዘኛ መስፈርት፣ በክፍል 3 የቦርድ ግምግማ አካሄድ መስፈርትና ክብደት፣ በክፍል 4 የዋና ሥራ አስፈፃሚ የግምግማ አካሄድ መስፈርትና ክብደት፣ በክፍል5 የማበረታቻ ክፍያ እና የእርምት እርምጃ አወሳሰድ፡ በክፍል 6 ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን በሜረሻም ይህንኑ ለመተግበር የማያስችሉ ልዩ ልዩ ፎርሞች በአባሪነት ተያይዘው ቀርበዋል፡፡