የመመሪያ መለያ: 931/2015
ቀን: መስከረም 26፥ 2015 ዓ.ም.
Language: Amharic

ጥሬ ገንዘብ፣ወርቅ እና የውጭ ሀገር ገንዘብ የመያዝና የማዘዋወር፣ ገንዘብ የማስተላለፍ የሀዋላ ስራ እንዲሁም ሀሰተኛ የገንዝብ ኖት ጋር በተያያዘ የሚፈጸም ሕገ ወጥ ድርጊት መረጃ አሰጣጥ፣ አያያዝ እና የወሮታ ክፍያ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 931/2015

የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ገንዘቦችን እንዲሁም ወርቅን ከተፈቀደው መጠን በላይ ህገወጥ በሆነ እና ባልተገባ መልኩ ይዞ የመገኘት እና የማዘዋወር ስጋት እንዲሁም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ፣

ወርቅ፤ ህገወጥ ገንዘብ፣ እንዲሁም ሀሰተኛ የገንዝብ ኖት ይዞ ከመገኘት እና ከማዘዋወር ጋር በተያያዘ እንዲሁም ህገወጥ በሆነ መንገድ ያለፈቃድ ገንዘብ የማስተላለፍ የሀዋላ ስራ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በተገቢው መንገድ እና በመረጃ በመታገዝ መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ እና ለዚህም አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ ጠቋሚዎች እና ያዦች ከተግባራቸው ጋር የተመጣጠነ የማበረታቻ ወሮታ ሊከፈላቸው የሚገባ በመሆኑ፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ(እንደተሻሻለ) አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 21(5(ለ) እና አንቀጽ 27(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

National Bank Of Ethiopia

Similar Directives