የኮሮና ቫይረስ በዓለም ዓቀፍና በሀገረ ደረጃ እየተሰራጨ ያለና በዓለም ዓቀፍ ጤና ተቋም በወረርሽኝ ደረጃ የተፈረጀ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በሽታ ህብረተሰቡ ላይ የበለጠ አደጋ ከማድረሱ በፊት አስቀድሞ መከላከል አስፈለጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የኮሮና ቫይረስ ግበዓቶች ለማምረት፣ ለማስመጣትና ለማከፋፈል የሚፈልግ አካል ቁጥጥር የተቀላጠፈና ህብረተሰቡ በቀላሉ ምርቶቹን በገበያ ላይ በበቂ አቅርቦት እንዲያገኝ ለማድረግ የቁጥጥር ሂደቱ ቀልጣፋ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የኮሮና ቫይረስ ግበዓቶች የማምረት፣ ማስመጣት፣ በጅምላ የማከፋፈል ተግባር አግባብነት ባለዉ ባለሙያ ኃላፊነት እንዲከናወን ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ የተጠበቀ የኮሮና ቫይረስ ግብዓት ለገበያ እንዲቀርብ በማድረግ የህብረተሰቡን ጤና ማስጠበቅ በማስፈለጉ፤
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71(2) መሠረት ይህን ጊዜያዊ የአሠራር መመርያን አውጥቷል፡