የመመሪያ መለያ: 45/2013
ቀን: የካቲት 1፥ 2009 ዓ.ም.
Language: Amharic

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸከርካሪ ማቆሚያ መሰረት ልማት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 45/2013

በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት ከሚስተዋሉ መጠነ ሰፊ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ችግሮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው፤ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራና አጠቃላይ የአሠራር ሂደት ነው። በትራንስፖርት ዘርፍ ትራንስፖርትና የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የማይነጣጠሉ መሠረታዊ የሆኑ ጉዳዮች ናቸው። የመንገድ ላይና ከመንገድ ውጪ ያሉ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች እጥረትና የአስተዳደር ችግሮች በሰፊው የሚስተዋሉ ሲሆን ተጠቃሚዎቹም ተሽከርካሪዎች ለማቆም ከቦታ ቦታ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ ተጨማሪ አሉታዊ ተጽዕኖ በመፍጠር ያለውን ወቅታዊ የትራፊክ መጨናነቅ ችግር የበተጠ እንዲባባስ አድርጎታል።

የከተማውን የትራፊክ ፍሰት ለማሳለጥና ተደራሽ ለማድረግ በከተማው አስተዳደር እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት መካከል ደረጃውን የጠበቀና ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆኑ የተሽከርካሪ ማቆሚያ /ፖርኪንግ/ መሰረተ ልማቶች መገንባትና ማስፋፋት አንዱ በመሆኑና የከተማው አስተዳደር በትልቅ ወጪ የተለያዩ የተሸከርካሪ ማቆሚያ እያለማ መሆኑ ይታወቃል፤

እነዚህ የለሙ እና በመልማት ላይ የሚገኙ የተሽከርካሪ ማቆሚያ መሰረተ ልማቶች የታለመላቸውን ዓላማ ይመቱ ዘንድ የሚተዳደሩበትን ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በከተማችን ለሚገኙ ስራአጥ ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር ከተማው ውስጥ ያሉ ወጣቶችን በተሽከርካሪ ማቆምያ አስተዳደር ስራ ላይ በማሰማራት ስራውን በአግባቡና በኃላፊነት እንዲሰሩ ለማደርግ በማስቻል እረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ተብሎ በመታሰቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 43/2007 አነቀፅ 47 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን በከተማዋ አስተዳደር ወጪ የተገነቡት የተሸከርካሪ ማቆሚያ መሰረተ ልማት አስተዳደር መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ትራፊክ አስተዳደር ባለስልጣን

የአዲስ አበባ ትራፊክ አስተዳደር ባለስልጣን

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 1÷2018
የገቢዎች ሚኒስቴር
Ministry of Revenues