የመመሪያ መለያ: 149/2016
ቀን: የካቲት 18፥ 2016 ዓ.ም.
Language: Amharic

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጭነት፤ ማሽነሪዎችን እና መሰል ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 149/2016

በአዲስ አበባ ከተማ በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓታት ላይ ለሚታየው ከፍተኛ የትራፊክመጨናነቅና አደጋ እንዲሁም የከባቢ አየር ብክለት የደረቅና ፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አስተዋጽዖ የጎላ በመሆኑ እነዚህ ተሸከርካሪዎች ወደ ከተማዋ መግባት የሚችሉበትንና በከተማው ውስጥ የሚንቀሳቀሱበትን ሰዓት በመወሰን ችግሮቹን መቅረፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በሰዓት መገደቡ ፍሰቱን ከማሳለጡም በተጨማሪ በዚህ መመሪያ እንቅስቃሴያቸው የተወሰነላቸው ተሸከርካሪዎችም አገልግሎታቸውን በተቀላጠፈና ወጪን በሚቀንስ መልኩ ማከናወን እንዲችሉ አዎንታዊ ሚና የሚኖረው በመሆኑ፤

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጭነት፣ ማሽነሪዎችን እና መሰል ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 38/2013 ላይ የሚስተዋሉ ለአፈፃፀም እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለመቅረፍ መመሪያውን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ (5) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Transport Bureau

Similar Directives

መጋቢት 30÷2018
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን
Petroleum and Energy Authority
መጋቢት 30÷2018
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን
Petroleum and Energy Authority
መጋቢት 30÷2018
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን
Petroleum and Energy Authority