በአዲስ አበባ አስተዳደር መንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሰለሚቀጠሩ ጊዜያዊ (ኮንትራክት) ሠራተኞች አቀጣጠር ፣ መብቶችና ግዴታዎች በግልጽ እንዲቀመጥ በማስፈለጉ ፤
በጊዜያዊ ሠራተኞች ምልመላና መረጣ በችለታ ፣ በግልጽነት ከአድሎ ነፃ በሆነ ውድድር ላጁ እንዲመሠረት ለማድረግ፤
በሁሉም ከተማው አስተዳደር መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግልጽ የሆነ አፈፃፀም እንዲኖር ለማድረግ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 6/2000 አንቀጽ 23/3 መሠረት ይህ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ኤጀንሲ ወጥቷል።