ነባር ኢንቨስትመንታቸውን የሚያስፋፉ ወደም የሚያሻሽሱ ባለሀብቶች ከማስፋፊያው ወይም ከማሻሻያው የሚያገኙት ተጨማሪ ገቢ ከኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ጋር የተያያዘውን ሰንጠረዥ መሠረት በማድረግ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት እንደሚያገኙ በሚኒስቴሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517/2014 አንቀጽ 5 የተደነገገ በመሆኑ፤
ለነባር ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ወደም ማሻሻያ የሚውሱ የካፒታል እና የግንባታ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ለማስገባት የሚቻሰው ባለሃብቱ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰኑ ማስረጃዎችን ሲያቀርብ እንደሚሆን በሚኒስቴሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517/2014 አንቀጽ 12(5) የተመሰከተ ሰስሆነ፤
በሚኒስቴሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517/2014 አንቀጽ 5 እና 12(5) የገንዘብ ሚኒስቴር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚከተለውን መመሪያ አውጥቷል፡፡