የመመሪያ መለያ: 723/2013
ቀን: የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

5ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት የኤግዚቢሽን ዝግጅት መመሪያ ቁጥር 723/2013

በኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የከተማ ነዋሪዎችንና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት የከተማ ልማት ፖሊሲውን እና የከተማ ልማት ፕሮግራሞችን ትግበራና ስኬት ማፋጠን ይቻል ዘንድ አመታዊ የከተሞች ሣምንት የተሰየመ ሲሆን የኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት በተለያዩ ከተሞች አስተናጋጅነት በየአመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡

ከኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት አበይት ክንውኖች መሀከል ከተሞችን የማስተዋወቅ ስራ አንዱ ነው:: የኢትዮጵያ ከተሞችም ባለፉት ዓመታት በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ከፍተኛ ዕድገት ያስመዘገበበትና ለሃገራዊ ምጣኔ ሃብት የሚሰጡት ግብዓት ከፍ ያለበት ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን ይህም ከተሞች ለኢንቨስትመንት፤ ለገበያ፣ ለቱሪዝም ወዘተ በራቸውን ክፍት ማድረግና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ያገኙት ውጤት ነው:: በቀጣይነትም ከተሞቻችን እርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ከዓለም ከተሞችም ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ውድድር ከተሞች ዕድገታቸውን ለማፋጠንና የነዋሪዎቻቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ከሚያደርጉት ጥረት በተጨማሪ ብቃት ያለው ራስን የማስተዋወቅ (professional city marketing) ስራን የሚጠይቅ ነው፡፡ ስለዚህም ከተሞች ከመቼውም ይበልጥ በተደራጀና ዓለም ዓቀፍ የጥራት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ራሳቸውን የማስተዋወቅ እና የመሸጥ ስራን አጠናክረው ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት ይህንን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የከተሞቻችንን ራስን የማስተዋወቅ ስራ ለማገዝ ይቻል ዘንድ አገር አቀፍ የኢትዮጵያ ከተሞች ኤግዚቢሽንን በፕሮግራሞቹ አካቷል፡፡

ይህ መመሪያ የኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት ኤግዚቢሽንን በሚመለከት ለተሳታፊ ከተሞች ጠቃሚ መረጃ በመስጠት አንዲሁም የአዘጋጆችን፣ የተባባሪዎችን እንዲሁም የተሳታፊዎችን ሚና በመለየት በባህር ዳር ከተማ ለአምስተኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ኤግዚቢሽን የሚመራበትን ስርኣት ለመደንገግ የተዘጋጀ ነው፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

Ministry of Urban Development and Construction

Similar Directives