የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትህ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መመዘኛ ሥርዓት እና የዐቃብያነ ህግ የሰው ሀብት መረጃ አያያዝ ስርዓትን የሚያዘምን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

Ministry of Justice and Ethiopian Airlines Sign Agreement to Upgrade Employee Performance and Legal HR Management Systems

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ሰራተኞች መመዘኛ ሥርዓት እና የዐቃብያነ ሕግ የሰው ሀብት መረጃ አያያዝ ሲስተምን ማዘመን የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርዓቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለምአንተ አግደው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኃላፊ አቶ ጌትነት ታፈሰ አካሂደዋል፡፡

የፊርማ ስነ-ስርዓቱን ካካሄዱ በኋላ ተቋማቱን ወክለው ፊርማቸውን በመግባቢያ ሰነዱ ላይ ያሳረፉት ኃላፊዎች መልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡ በፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ አለምአንተ አግደው በንግግራቸው ተቋሙ የሀገሪቱን ህጎች ከማርቀቅና የወጡ ህጎች በትክክል መተግበር አለመተግበራቸውን ከመከታታል አንጻር ከፍተኛ ኃላፊነት እንደተጣለበት አመላክተው ይህን የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት የሚያስችልና ሠራተኛውን የስራ አፈጻጸም በትክክል የሚመዝን፣ በቴክኖሎጂ የታገዘና ስራን የሚያሳልጥ መተግበሪያ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለውን ልምድ መውሰድ እንዳስፈለገ ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም ተቋሙ እንደየ ስራ ክፍሉ የስራ ባህሪ አግባብነት ያለው መመዘኛ በማዘጋጀት እያንዳንዱን ስራ በየቀኑ መመዘን ለማስቻል ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር የሰራተኞች መመዘኛ ሥርዓት እና የዐቃብያነ ሕግ የሰው ሀብት መረጃ አያያዝ ስርዓት የሚዘምንበትን የጋራ መግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ተናግረው መተግበሪያው ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ ለስራ ቅልጥፍናና ውጤታማነት የጎላ ሚና እንደሚኖረውም ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮጲያ አየር መንገድ በኩል የአየር መንገዱ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኃላፊ አቶ ጌትነት ታፈሰ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም አየር መንገዱ በጉዳዩ ላይ ያለውን ልምድ ለ15 የመንግሥት ተቋማት ያጋራ መሆኑን አስታውሰው በተመሳሳይ ፍትሕ ሚኒስቴርም የአሠራር ስርዓቱን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም በመቻላቸው ደስታ እንደተሰማቸው እና በቀጣይ በስምምነቱ መሠረት ተገቢው ድጋፍ ሁሉ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚደረጉ አረጋግጠዋል፡፡

Tagged Under: Employee Performance Ethiopian Airlines
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች