በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት ሂደት ዙሪያ ለሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ የተላለፈ ግብዣ
በኢትዮጵያ የሚዲያ ስራ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ፈቃድ ላላቸው የሚዲያ ተቋማት ሁሉ የተላለፈ ጥሪ
እለተ አርብ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት አንደኛ ፎቅ የሽግግር ፍትሕ የሕዝብ ምክክር ሂደት አፈጻጸም፤ በሕዝብ አስተያየት ግብዓቶች የተመላከቱ ዋና ዋና ግኝቶች እና በባለሙያዎች ቡድኑ ምክረ ሃሳብ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ የሚዲያ ስራ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ፈቃድ ያለው እና በመግለጫው ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ማንኛውም የሚዲያ ተቋም በእለቱ ከላይ በተገለጸው ቦታ በመገኘት እና መረጃዎችን በመያዝ የዜና ሽፋን እንዲሰጠን እየጋበዝን ወደ ተቋሙ የሚመጡት የሚዲያ ተቋሙ ባለሙያዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የመታወቂያ ካርድ ይዘው እንዲመጡ እናስታውቃለን፡፡
የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች ቡድን