የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ ከተሰጡት ተግባር እና ኃላፊነቶች መካከል አንዱ የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ማሳድግ ነው፡፡ ይህን ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ መንገዶች የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሠረትም ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ ድጋፍ ‹‹ንቃተ ሕግ›› በሚል ርዕስ ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 5:30_6:00 ሰዓት በፋና ሬድዮ 98.1 ኤፍ ኤም እና በፋና ብሔራዊ ራዲዮ ዘወትር ሀሙስ ምሽቱ ከ12፡30-1፡00 ሰዓት፤ እንዲሁም በመደበኛ በጀት /በራስ አቅም/ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዲዮ ‹‹የሕግ ነገር›› ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 3:05_4:00 ሰዓት አስተማሪ የሆነ የሕግ ጉዳዮችን ይዞላችሁ ይቀርባል፡፡በመሆኑም ፕሮግራሙን በመከታተል ሀሳብ አስተያየቶን ይስጡን፣ ቢቀርቡልን የምትሏቸውን የሕግ ርዕሰ ጉዳዬች ይላኩልን፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት