የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት በፍትሕ ሚኒስቴር የሚሰጡ ምክረ ሃሳቦችን በመተግበር የመንግሥት እና የሕዝብን ፍትሐብሔራዊ ጥቅም ማጠበቅ እንደሚገባቸው ተገለፀ

Federal Institutions Urged to Implement Ministry of Justice Recommendations to Protect Government and Public Interest

በፌዴራል የመንግሥት ተቋማት የፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ ክትትል ግኝት ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከፌደራል መንግሥት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች ጋር መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት ተካሄደ፡፡

የውይይት መድረኩ በ2017 በጀት ዓመት በፌዴራል የመንግሥት ተቋማት ላይ በተደረጉ የፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ ክትትል የተገኙ ግኝቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ በቀጣይ ተጠናክረው ሊቀጥሉ የሚገባቸውን ጉዳየች አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች በማሻሻል እና የተሻለ የአሰራር ቅንጅትን በመፍጠር የመንግሥት እና የሕዝብን ፍትሐብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በውይይት መድረኩ የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት የፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ ክትትል ግኝት ሪፖርት እና የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት እርስ በእርስ ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮች የውሳኔ አሰጣጥ እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት የተስተዋሉ ችግሮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በሪፖርቱ የተቋማት ክትትል ዓላማ፣ በክትትል የተገኙ ግኝቶች ፣በክትትል ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት በክትትል የሚሰጡ ምክረ ሃሳቦችን በመተግበር እንዲሁም ከፍ ያለ ዋጋ ባላቸውና በይዘታቸው ውስብስብ በሆኑ ውሎች ላይ ከድርድር ጀምሮ ውሉ እስከሚፈፀምበት ድረስ የፍትሕ ሚኒስቴር ተሳታፊ እንዲሆን በማድረግ የመንግሥት እና የሕዝብን ፍትሐብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ እደሚገባ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት እርስ በእርስ ባልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮች የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ በተቋማት በኩል የሚስተዋሉ ችግሮች ትኩረት ተሰጥቶ ሊስተካከሉ እንደሚገባ በውይይት መድረኩ ተገልጿል።

በውይይቱ የፍትሕ ሚኒስቴር ከሚያከናውናቸው ስራዎች መካከል የመንግሥት እና የሕዝብን ፍትሐብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ አንዱ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ በዚህም የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት አጠቃላይ የፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ ክትትል እና ድጋፍ እንዲሁም ተቋማት የሚቀርቡባቸውን የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ክሶች ድርድር በማድረግ በስምምነት እንዲያልቁ ጥረት በማድረግና ተቋማትን ወክሎ በመከራከር የሕዝብ እና የመንግስትን ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ተጨባጭ ዉጤት መታየቱ ተገልጿል፡፡

Tagged Under: and healthcare administration and control authority ethiopian federal government ethiopian federal justice system ethiopian federal ministry of justice Ethiopian Ministry of Justice fdre ministry of justice federal Federal and Regional Governments federal government institutions federal institute of justice and law Federal Institutions federal justice and law institute federal ministry of justice Government government law and justice services sector institution institutions interest itu Justice ministry ministry of public service and human resource development pro public Public interest recommendations res
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች