የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴርና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወጎኖች የሰብዓዊ ድጋፍ አደረጉ

FDRE Ministry of Justice and Civil Society Organizations Authority Provide Humanitarian Aid to Victims of Landslide Disaster in Kencho Kebele, Geze Gofa Woreda, Gofa Zone

የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን በአካባቢው በደረሰው ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በተጠሪ ተቋማትና በራሳቸው ስም ገልፀዋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በደረሰው ልብ የሚሰብር አደጋ ጉዳት የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን ገልፀዋል።

የፍትሕ ሚኒስቴርና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አጋር አካላትን በማስተባበር ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ( Menschen fűr Menschen) ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በሚገመት ወጪ የተገኘን የአልባሳት ፣ የበቆሎ ዱቄት ፣ የምግብ ዘይት ፣ የሕፃናት አልሚ ምግቦች ፣ አተር እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶቁሶችን በአይነት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትሕ ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ አቤነዘር ተረፈ እና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በተገኙበት ለእለት ደራሽ የሚሆን ሰብዓዊ ድጋፍን አስረክበዋል።

የMenschen fűr Menschen የኢትዮጵያ ተጠሪ የሆኑት አቶ ይልማ ታዬ በደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት ድርጅታቸው ማዘኑን ገልጸው የተደረገው ድጋፍ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይዳረጉ የሚያግዝ የአንድ ወር ቀለብ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ለተጎጂዎች የሚውል 300 ሺህ ብር በዞኑ በተከፈተ አካውንት ገቢ አድርገዋል።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ለተደረገላቸው ሰብዓዊ ድጋፍ ተቋማቱን በዞኑ ሕዝብና ጉዳት በደረሰባቸው ወጎኖች ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚ/ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ተጠሪ ተቋማትንና ሌሎች የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር ሀላፊነቱን እንደሚወጣ ገልፀዋል።

Tagged Under: Authority • civil • civil society organizations authority • clothing • democratic • disaster relief • dr. ermias yemaneberhan • emergency response • FDRE • federal • federal democratic republic of ethiopia (fdre) • food aid • geze gofa woreda • gofa • gofa zone • Humanitarian Aid • kencho kebele • Landslide • organizations • republic • society • zone
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች