በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር እንዲሁም ተጠሪ ተቋም በሆነው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች አማካኝነት የበጎ ፍቃድ የደም ልገሳ ተካሄደ

Voluntary Blood Donation Held by Leaders and Employees of the FDRE Ministry of Justice and its Affiliate, the Civil Society Organizations Authority

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴርና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት ከደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት በሚኒስቴሩ ዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በበጎ ፍቃድ የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡

“ደም ይለግሱ ህይወትን ያድኑ” በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃድ የደም ልገሳ ፕሮግራም የተካሄደው በየአመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጀው የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የፍትሕ ሚኒስቴር እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት አመራር እና ሰራተኞችን በማሳተፍ የመንግሥት የልማት ኢኒሼቲቮችን ለማሳካት ተቋማቱ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ያለመ ነው፡፡

በጤና ሚኒስቴር የደም ልገሳና ህዋስ ባንክ አገልግሎት የትምህርትና ቅስቀሳ ባለሙያ ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ በቦታው ተገኝተው እንዳሉት ደም መለገስ ከራስ አልፎ ለሌሎች ሰዎች መኖር ማለት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ከመቀበል መስጠት እንደሚሻል አውስተዋል፡፡

ደም መለገስ በየሆስፒታሉ የኩላሊት እጥበት የሚደረግላቸው ፣ ከባድ የቀዶ ጥገና የሚሰራላቸው ፣ የካንሰር ተማሚዎች ፣ የጨረር ህክምና የሚደረግላቸው ፣ ከባድ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ግለሰቦች እና በወሊድ ምክንያት ደም የሚፈሳቸው እናቶች በደም ማጣት ምክንያት ለድንገተኛ ሞት እንዳይዳረጉ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

ደም ስንለግስ ደም የሚያስፈልገው ሰው ከእኔ ቤተሰብ አንዱ ቢሆንስ ፣እኛም ራሳችን ምን ሊገጥመን እንደሚችል ስለማናውቅ ጤነኛ በሆንበት ወቅት ደም መለገስ ከራሳችን አልፈን ለሌላ ሰው መኖር በበጎ ፍቃደኝነት የሚከናወን ሰብዓዊ አገልግሎት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሲስተር አሰጋሽ በገለፃቸው ጤነኛ የሆነ ሰው ፣ 45 ኪሎ ግራም ክብደት የሞላው እና ዕድሜው ከ18 እስከ 65 ዓመት የሆነው ሰው በየሶስት ወሩ አንድ ጊዜ እንዲሁም በዓመት አራት ጊዜ ደም መለገስ የሚችል መሆኑን አውስተዋል፡፡

በመጨረሻም “በሚተካ ደም የማይተካውን ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት እንታደግ”ሲሉ ሲስተር አሰጋሽ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በቀጣይ ሁለት ቀናትም የተቀሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት አመራር እና ሰራተኞች አማካኝነት የበጎ ፍቃድ የደም ልገሳ ፕሮግራም እንደሚያካሂዱ ተገፁዋል፡፡

Relevant Departments and People
Tagged Under: Authority bank blood blood bank service blood transfusion civil civil society organizations authority democratic donation FDRE federal federal democratic republic of ethiopia (fdre) Health Ministry maternal health organizations Public Health republic Service society voluntary
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች

No data was found