የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አስተዳደራዊ ዳኝነት ችሎት የውሳኔ ጥራትን ለማረጋገጥ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገለፀ

The Trade Competition and Consumer Protection Administrative Tribunal of the FDRE Ministry of Justice States its Planned Efforts to Ensure Decision Quality

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አስተዳደራዊ ዳኝነት ችሎቱ በሚሰጣቸው ውሳኔዎች ጥራትን ለማረጋገጥ ታቅዶ በመሰራቱ ችሎቱ በግማሽ ዓመት ውስጥ ውሳኔ በሰጠባቸው 8 መዝገቦች ላይ ይግባኝ ቀርቦባቸው 7ቱ ውሳኔዎች እንዲጸኑ እንደተደረጉ ተጠቆመ፡፡

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አስተዳደራዊ ዳኝነት ችሎት የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ መብትን አስመልክቶ የተከለከሉ ተግባራትን በፈፀሙ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃና ቅጣት የመወሰን ፣ተገቢ ባልሆነ የንግድ ውድድር ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎች ለደረሰባቸው ጉዳት አግባብ ባለው ሕግ እንዲካሱ የማድርግ እና ከነጋዴው በገዙት የንግድ እቃ ወይም አገልግሎት አመካኝነት ጉዳት ለደረሰባቸው ሸማቾች አግባብ ባለው ሕግ መሠረት እንዲካሱ የማድርግ ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 813/2006 መሠረት እንደተሰጠው የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሆኑት አቶ ኪዳኔ ፀጋዬ ገልፀዋል፡፡

አቶ ኪዳኔ አያይዘውም ችሎቱ በ6 ወራት ውስጥ ከሸማቹ የቀረቡ በድምሩ 238 679 / ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺ ሰድስት መቶ ሰባ ዘጠኝ / ብር ግምት ያላቸው የፍትሐ-ብሄር ክሶች ቀርበው ሁሉም በተቀመጠላቸው ጊዜ ገደብ ውሳኔ እንደተሰጠባቸው እና ነጋዴ በሌላ ነጋዴ ላይ ያቀረባቸው ጠቅላላ የዋጋ ግምታቸው 1,100,000 ብር የሚያወጡ ሁለት መዝገቦች ላይ ውሳኔ እንደተሰጠ እንዲሁም በጸረ-ውድድር ተግባራት ቀጠሮ ላይ የነበሩ 4 መዝገቦች ውሳኔ እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡

ውዝፍ መዝገቦችን የማጥራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ሰብሳቢ ዳኛ የገለፁ ሲሆን የውሳኔ ጥራትን ለማረጋገጥ ታቅዶ በመሰራቱ በ8 ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ ቀርቦባቸው 7ቱ ውሳኔዎቻችን እንዲጸኑ ሆነዋል ብለዋል፡፡

Relevant Departments and People
Tagged Under: administrative administrative sanctions Administrative Tribunal antitrust antitrust law appeals caseload Commercial Law competition consumer Consumer Protection consumer rights court decisions decision decisions Dispute Resolution fdre ministry of justice judicial efficiency Justice legal Legal Decisions legal remedies ministry protection quality Trade Trade Competition tribunal
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች