የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና አምስቱ ተጠሪ ተቋማት የጋራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብ ቀጥሏል

The FDRE Ministry of Justice and its Five Affiliated Institutions Continue Joint Tree Planting Program

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና አምስቱ ተጠሪ ተቋማት የጋራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብ ቀጥሏል፡፡

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና አምስቱ ተጠሪ ተቋማት፤ የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን፣ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት፣ የሕግ እና ፍትሕ ኢንስቲቲዩት፣ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን እና የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አመራሮች እና መላ ሰራተኞች በጋራ በመሆን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግበርን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚሁም መሠረት ሀምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ አሳግርት ወረዳ ታሞ ቀበሌ እንዲሁም በዛሬው እለት ሀምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም በቡሾፍቱ ከተማ የተራቆቱ ስፍራዎችን በችግኝ የመሸፈን ስራ ሰርተዋል፡፡ በሁለቱም ስፍራዎች በድምሩ ከ4,000 በላይ የተመረጡ ችግኞችን መትከል ተችሏል፡:

ተቋማቱ ከሳምንት በፊትም ተቋማቱ አመራሮችን እና መላ ሠራተኛውን እንዲሁም የአካባውን ማኅበረሰብ በማሳተፍ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ አይ ሲ ቲ ፓርክ አካባቢ በሚገኘው ሰፊ የመንገድ አካፋይ ቦታ ላይ ከ5,000 ያላነሱ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች መትከላቸው ይታወቃል፡፡ተቋማቱ በቀሪ ጊዜያትም በሌሎች በተመረጡ አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብ የሚያካሂዱ ሲሆን በክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎችም ላይ ለመሳተፍ የጋራ ዕቅድ በማውጣት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡

Relevant Departments and People
Tagged Under: Affiliated Institutions Community Service Environmental Protection Tree Planting
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች

No data was found