በቅርቡ ፍትህ ሚኒስቴር ለተቀላቀሉ ዐቃቤያነ ህግ ለአምስት ቀናት ሲሰጥ የነበው ተግባር ተኮር ስልጠና ተጠናቀቀ

The five-day task-oriented training provided to prosecutors who recently joined the Ministry of Justice has been completed.

በ2015 እና በ2016 በጀት ዓመት ለተሾሙ ዐቃቤያነ ሕግ በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ተግባር ተኮር በሆነ ሁኔታ የወንጀል ምርመራ ፣ ክስ ዝግጅት እና ችሎት ክርክር ላይ ያተኮረው የ1ኛ ዙር ሥልጠና በትላትናው እለት ተጠናቋል።

በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው የመዝግያ ንግግር እና የሰራ አመራር የሰጡት የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃን ሰልጣኞች በሥልጠና ያገኙትን እውቀት እና ክህሎት በጥብቅ ስነ-ምግባር ስራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የ2ኛ ዙር ሥልጠና በሚቀጥለው ሳምንት በተመሳሳይ መልክ እንደሚሰጥ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: Advocacy attorney Attorney General Capacity Building court criminal Criminal Investigation Criminal Prosecution general Investigation Judicial Training legal Legal ethics Legal Reform legal skills training Legal Training professional professional development Prosecution Prosecutor Prosecutor training prosecutors office reform skills Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች