ማስታወቂያ

Announcement

ፍትሕ ሚኒስቴር በፍትሐ ብሄር ጉዳዮች ዙሪያ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት እንደሚሰጥ ያውቁ ኖሯል?

ፍትሕ ሚኒስቴር በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐ ብሄር ክስ መሥርተው ለመከራከር የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን እንዲሁም የገንዘብ አቅም የሌላቸውን የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ዜጎችን በመወከል ክርክር በማድረግ መብታቸውን እንዲያስከብር በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(4) (ሠ) እና (ረ) መሠረት ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡

ይህንኑ ኃላፊነት ለመወጣት ድሬዳዋን ጨምሮ በአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ምድብ የፍትሕ ሚኒስቴር ጽ/ቤቶች አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችል አሠራር በመዘርጋት የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በነጻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን የሚሰጠው አገልግሎት ዜጎች በገንዘብ እጦት መብታቸው ሳይከበር እንዳይቀር ለማድረግ ያለመ እና በተለይም ተጋላጭ የሚባሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።

አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋይ እንዲያሟላ የሚያስፈልገው ቅድመ ሁኔታ ከምትኖርበት ከሚኖርበት አካባቢ አስተዳደር መስሪያ ቤት የገንዘብ አቅም የሌላት/የሌለው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ይዞ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት መቅረብ ሆኖ አገልግሎት ከሚጠየቅበት ጉዳይ ጋር የተያያዙ ማስረጃዎች (ካሉ) ተያይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

አገልግሎቱን ወይም ስለ አገልግሎቱ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ ወደሚገኘው የፍትሕ ሚኒስቴር ምድብ ጽ ቤት በመሄድ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያስታወቅን ይህ ማስታወቂያ ለማይደርሳቸው ለሌሎች አገልግሎቱን ማግኘት ለሚሹ ወገኖቻችን ይህን መልዕክት በማስተላለፍ ለዜጎች ፍትሕ ማግኘት መብት የበኩሎን አስተዋጾ እንዲያበረክቱ እንጠይቃለን።

Relevant Departments and People
Tagged Under: Access to Justice addis ababa aid bono cases children civil civil cases Courts Dire Dawa disabled disabled persons elderly eligibility criteria federal Federal Courts legal Legal Aid Legal representation populations pro pro bono legal services public announcement Services vulnerable vulnerable populations women
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች

No data was found