በመገናኛ ብዙሃን በቀረበ ዘገባ መልካም ሥሜና ክብሬ በሃሰት ወይም በአሉታዊ ጎኑ ተጎዳብኝ ያለ ሰው ምን መብት አለው?

ማውጫ

Share this Article

በዛሬው “ከነጋሪት ገጾች” አምዳችን በአዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ውስጥ ከመገናኛ ብዙሃን መብቶች እና ግዴታዎች መካከል አንዱን ነቅሰን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

በዚሁም መሠረት በመገናኛ ብዙሃን በቀረበ ዘገባ መልካም ሥሙና ክብሩ በሐሰት ወይም በአሉታዊ ጎኑ ተጎዳብኝ ያለ ማንኛውም ሰው በተመሳሳይ ሚዲያ፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ በግልፅ እና ያለክፍያ እርማት የመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን ዘገባው የቀረበው በቴሌቪዠን ወይም በሬዲዮ ፕሮግራም ላይ የነበረ ከሆነ እርማቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ባሉ 5 ቀናት ውስጥ መተላለፍ አለበት። ይህ ካልሆነ የእርማት መብቱን የተነፈገ ማንኛውም ሰው የፕሮግራሙ አዘጋጅ ተገዶ መልሱን እንዲያወጣለት ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡ ይሁንና የእርማት ጥያቄው ነገሩ ከተሰራጨበት ቀን ጀምሮ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የቀረበ እንደሆነ ብቻ የሚስተናገድ ስለመሆኑ አዋጁ ይደነግጋል፡፡

ዋቢ፡- የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 48