በዛሬው ‘ከነጋሪት ገፃች’ አምዳችን “ብርበራ”ን የሚመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ልንጠቁም ወደድን
- ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር ቤቶን መበርበር አይችልም።
- ከፍርድ ቤት በተለየ ካልታዘዘ በቀር ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።
- ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም።
- መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል።
ምንጭ፡- የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ