ማንም ሰው ከወንጀል ድርጊቱ አትራፊ መሆን የለበትም!

ማውጫ

Share this Article

በዛሬው `ከነጋሪት ገጾች` አምዳችን በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀልን በተመለከተ ጠቃሚ መረጃ ልናጋሮት ወደድን

ማንኛውም ሰው ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ እየተገባው ንብረቱን የተረከበ፣ በይዞታው ያደረገ ወይም የተጠቀመ እንደሆነ፤ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ንብረቱ የሚወረስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ10 ዓመት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 100,000 በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ ህጉ ይደነግጋል።

በተመሳሳይ አንድን ንብረት፤ ቤት ወይም መኪና ወይም ጥሬ ገንዘብ በማንኛውም መንገድ ስለ ገንዘቡ ምንጭ አስፈላጊ ማጣራት ሳያደርጉ ስመ ሀብትን በራስ በማድረግ እንዲሁም በስም በተከፈተ የባንክ አካውንት ገንዘብ ገቢ እንዲደረግ በመፍቀድ በወንጀል ተጠያቂ መሆን አለና አንድን ንብረት ከመረከባችን እና ከመያዛችን ወይም ከመጠቀማችን አስቀድመን ስለ ንብረቱ ተገቢውን መሰጣራት እና ከየት መጣ፣ ምንጩ ምንድንነው መጠየቅ የሚለውን መለየት እና ማወቅ ነጻነትን ከሚያሳጣ የወንጀል ቅጣት ያድናል።

በአዋጁ የንብረቱ ምንጭ ሕገወጥ መሆኑን ለማስረዳት በተከሳሽ ላይ በአመንጪው (ህገ ወጥ ጥቅሙ የተገኘበት መነሻ ወንጀል) ወንጀል የጥፋተኛነት ፍርድ መሰጠቱ የግድ የሚያስፈልግ አለመሆኑ ደግሞ ሰዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስጠንቃቂ ጉዳይ ነው።

ምንጭ፡-በ ወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 የተወሰደ።