የፌዴራል ጠበቆች የዲስፕሊን ክስ አቀራረብ እና የክርክር ሥነ -ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 3/2017 መፅደቁን ያውቃሉ?

ማውጫ

Share this Article

በሀገራችን ጥራት ያለው የጥብቅና አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል እና አገልግሎቱን ለማዘመን የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 በሥራ ላይ መዋሉን ተከትሎ የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ የተሰጡትን ኃላፊነቶች ለመወጣት የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ቦርዱ በአዋጁ አንቀጽ 87 (1) ሥር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በፌዴራል ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች ላይ የሚቀርቡ የዲሲፕሊክ ክሶች አቀራረብ እና የክርክር ሂደቱ በግልፅ የሚመራበትን የሥነ-ሥርዓት መመሪያ አፅድቋል፡፡

መመሪያው የጠበቆች ዲስፕሊን ጉባኤ የተሰጠውን ኃላፊነት በተሟላ መልኩ ለመወጣት አጋዥ ሲሆን በተጨማሪም ለጉባኤው የሚቀርቡ አቤቱታዎችና ምላሾች ማካተት ያለባቸውን ይዘት እና በክርክር ሂደት የሚተገበሩ ሥነ-ሥርዓቶች ግልፅና ለሁሉም የታወቁ እንዲሆኑ በማድረግ የዲስፕሊን የክስ እና የክርክር አመራር ሂደቱ ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ተገማች እንዲሆን ማድረግ ያስችላል፡፡ ስለሆነም መመሪያው ወደ ሥራ መግባቱ ጉባኤው ኃላፊነቱን ወጥ በሆነ አሠራር ለመምራት፣ በአፈፃፀም ረገድ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና ፍትሐዊ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያግዝ ይሆናል፡፡

መመሪያው በሶስት ክፍሎች የተከፈለ እና በአጠቃላይ ሠላሳ ዘጠኝ አንቀጾች ያሉት ሲሆን በዋናነት በጠበቃ ወይም በጥብቅና ድርጅት ላይ የሚቀርብ የሥነ-ምግባር ጥፋት ክስ፣ የመከላከያ መልስ፣ የማስረጃ አቀራረብ እና የክርክር ሂደትን እንዲሁም የዲስፕሊን ጉባኤው የውሳኔ እና የቅጣት አሰጣጥ ሂደት በዝርዝር ደንግጓል፡፡

በመሆኑም የዲስፕሊን ክስ አቀራረብ እና የክርክር ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 3/2017 ከጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ መግባቱን በማወቅ ማናቸውም በሂደቱ የሚሳተፍ አካል እንዲገለገልበት ይጠበቃል፡፡ በዚህ መሠረት ሙሉ የመመሪያውን ይዘት በማወቅ እንድትገለገሉበት ለማስቻል ከዚህ በታች የተመለከተውን ሊንክ በመጫን ማግኘት የሚቻል መሆኑን ቦርዱ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

https://drive.google.com/…/157S7I…/view…

የፌደራል ጠበቆች አስተዳደር ቦርድ