የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በመከላከያ ሆስፒታል ተገኝተው የክረምት በጎ አድራጎት አካል የሆነውን የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናውነዋል።
በየ ዓመቱ እየተከናወነ ያለው የደም ልገሳ መርሐ ግብር የመተባበርና የመተጋገዝ ዋና ማሳያ መሆኑ በእለቱ ተገልፆ ደም ከመለገስ የበለጠ ልግስና እንደሌለም ተወስቷል።
በዚህ መርሐ ግብር ላይ የመከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ የፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ማለትም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት እና ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እንዲሁም የሰላም ሚኒስቴር የበላይ አመራሮችና ሠራተኞች በነቃ ሁኔታ ተሳታፊ ሆነዋል። በየዓመቱ የሚከናወነው ይህ የበጎ አድራጎት ተግባር የኅብረተሰባችንን የመተባበርና የመተጋገዝ ባህል በሚገባ የሚያጎላ መሆኑ በተከናወነው መርሐ ግብር ላይ ተገልጿል። ይህ ሰብአዊ የበጎ አድራጎት ተግባርም በቀጣይነት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።