በዛሬው “ከነጋሪት ገፆች አምዳችን” የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን በሚመለከት የሕግ ተጠያቂነትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ልናጋራ ወደድን
ህጻንን ለአካሉ ወይም ለዕድሜው በተጻረረ መልኩ ሥራ ማሰራት በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ነው።
የህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ማለት ህፃንን በሕግ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጭ ወይም ለህጻኑ አካል ወይም ዕድሜ በተጻረረ መልኩ ስራ እንዲሰራ ወይም አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ነው።
ማንኛውም ሰው ህጻናትን ለአካላቸው ወይም ለዕድሜያቸው በተጻረረ መልኩ ሥራ ያሰራ እንደሆነ ወይም እነዚህን መሰል የብዝበዛ ተግባራት የፈፀመ እንደሆነ ከ7 ዓመት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከ20 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
ብዝበዛው ቢጀመርም ባይጀመርም ህጻናትን ለብዝበዛ ዓላማ መመልመል፣ ማጓጓዝ፣ ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ፣ ማስጠለል፣ መደበቅ ወይም መቀበል በሰው የመነገድ ድርጊት ነው።
ምንጭ፡- አዋጅ ቁጥር 1178/2012 በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ