በዛሬው የነጋሪት ገጾች አምዳችን ማንነትን ለመደበቅ ስምን መለወጥ ስለሚያከትለው የወንጀል ተጠያቂነት ልንነግሮት ወደናል፡፡
ስንወለድ ሰው በመሆን ከምንጎናጸፋቸው የማንነት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ በፍትሐ- ብሄር ህጋችን ተደንግጎ የምናገኝው “ስም የማግኘት መብት ነው። በዚህም መሠረት ቤተሰቦች ለወለዱት ልጅ መጠሪያ ያወጡለታል፡፡
ይህ መጠሪያ የሰው ልጅ በህይወት ዘመኑ ከሌሎች ተለይቶ ይታወቅበታል፣ መብቱን ይጠይቅበታል፡፡ ይሁንና ይህንን በቤተሰብ የተሰጠን ስም ሰዎች በብዙ ምክንያት የሕግ አግባብን ተከትለው ለፍርድ ቤት ማመልከቻ አቅርበው ሊቀይሩት ይችላሉ፡፡ ልብ “ይበሉ በፍርድ ቤት” ነገር ግን ከዚህ ህጋዊ ስነ-ስርዓት ውጭ ማንም ሰው ማንነቱን ለመደበቅ ወይም አግባብ ካለው ባለሥልጣን ቁጥጥር ስር ለማምለጥ በህገ-ወጥ መንገድ የፈጠራ ስም ለራሱ የሰጠ፣ እውነተኛ ስሙን የለወጠ ወይም በዚያው ላይ ለራሱ ሌላ ስም የጨመረ ወይም በሌላ ሰው ስም የተጠቀመ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ በገንዘብ ወይም በማረፊያ ቤት እስራት እንደሚቀጣ የወንጀል ህጉ በግልጽ ይደነግጋል፡፡
ቢሆንም ማንነቱን ለመደበቅ ወይም አግባብ ካለው ባለሥልጣን ቁጥጥር ስር ለማምለጥ በማሰብ ሳይሆን የሙያ፣ የሥነጽሁፍ ወይም የፈጠራ ስም በልማድ የሚታወቅን የቅጽል ስም መጠቀም የሚያስቀጣ ተግባር አለመሆኑን መረዳትም ተገቢ ነው።
ከነጋሪት ገጾች