Tender ID:
Moj-NCB-W-0191-2016-PUR
Published on:
April 8, 2025 11:03 pm
Closing Date:
April 11, 2025 3:00 pm
Opening Date:
April 12, 2025 2:00 pm

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ከማስተገበር አንፃር ተልዕኮ ወስዶ የሕዝብ ንቃናቄ እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ የተለያዩ የህትመት ስራዎችን በመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት (Electronic Government Procurement System) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ስርዓት ድህረ-ገፅ www.egp.ppa.gov ላይ በመመዝገብ ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ማስታወቂያ በሲስተሙ ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቶች በሚጫረቱበት የህትመት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በአካል ማቅረብ ግዴታ መሆኑንና እያሳወቅን ሌሎች ዝርዝር መስፈርቶችን በሲስተሙ ላይ ይፋ በተደረገው የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ በሲስተም አየር ላይ ከዋለበት ቀን march 13,2025 ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ስለሚሆን ተጫራቾች በሲስተሙ በመመዝገብ መጫረትና የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ተጫራዎች ለተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የስልክ አድራሻ በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑነ እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- ቅ.ኡራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ባምቢስ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት የሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር 

ስልክ ቁጥር፡- +251-011-5-58-40-48