የመመሪያ መለያ: 689/2013
ቀን: ጥቅምት 1፥ 2006 ዓ.ም.
Language: Amharic

የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር የደረጃ አሰጣጥ መስፈርትና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 689/2013

ኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ስትሆን፣ እየተመዘገበ ካለው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጐት በከፍተኛ ደረጃ በማደግ ላይ ነው፡፡ እያደገ የመጣውን የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጐት በአግባቡ በመመለስ የግብርና ምርቶችና የፋብሪካ ውጤቶች ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ በማጓጓዝ ለተጠቃሚው የሚያደርሱ የትራንስፖርት ድርጅቶች፣ ኩባንያዎች፣ ማኀበራትና የግል ትራንስፖርተሮች አደረጃጀትና አሠራር በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲሁም በቂ የመረጃ ሥርዓት የተዘረጋለት ሆኖ አገልግሎት አሰጣጡ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ሆኖ እንዲራመድ ማድረግ ያስፈልጋል፣

የጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ በዉድድር ስርዓት ያልተጠናከረ በመሆኑ፤ ዘርፉ በቅልጥፍናና በጥራት ተከታታይ እድገት የማይታይበት በመሆኑ፤ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎቱ ለደላላ የተጋለጠ በመሆኑ፤ የአመለካከት ለውጥ የሚያመጣ አደረጃጀት ለመፍጠር፤ ልማቱን በሚጠቅም ሁኔታ የዘርፉን ዓቅም ለማሳደግ፤ የጭነት ትራንስፖርት በዋጋ ተዋዳዳሪ እዲሆን ለማስቻል፤

በተለይም ጭነት የማጓጓዝ አገልግሎት የሚሰጡ የትራንስፖርት ድርጅቶች፣ /ኩባንያዎች፣/ ማኀበራትና የግል ትራንስፖርተሮች ከዘልማዳዊ አሠራር ተላቀው በአገልግሎታቸው ብቃትና ጥራት ተለይተው እንዲሠሩ በማድረግ በዘርፉ ያላቸውን ጉልህ ሚና በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ እንዲያከናውኑ ማድረግና፣ የአገሪቱ ምርቶች በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል አደረጃጀት ፈጥረው ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን መውጣት ይኖርባቸዋል።በግልጽ የመለኪያ መስፈርቶች ላይ የተመሠረተ የውድድር ሜዳ በመፍጠር ጤናማ የአገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ፣ አገልግሎት በመስጠት ላይ የተሠማሩ ትራንስፖርተሮች ውስጣዊ አሠራራቸውን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በማጠናከር የተሽከርካሪዎች ስምሪት በጠንካራ አደረጃጀትና ሰው ኃይል እየታገዘ በሥርዓት የሚመራበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ አስፈልጓል።

በመሆኑም ይህ የድንበር ተሸጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ማኀበራትና ድርጅቶች አገልግሎት አሰጣጥ የደረጃ መሥፈርትና የአፈፃፀም መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

Ministry of Transport and Logistics

Similar Directives

ጳጉሜ 05፥2018
የትምህርት ሚኒስቴር
Ministry of Education
ነሀሴ 20፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን
Addis Ababa City Public Property Administration Authority