የመመሪያ መለያ: 711/2013
ቀን: የካቲት 9፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የለውጥና የልማት ቡድን አደረጃጀት መመሪያ ቁጥር 711/2013

በሚኒስቴር መስሪያቤታችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎቻችንን ስኬታማ ለማድረግና የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን በተሟላ መልኩ ለማሳካት የመፈፀም አቅማችንን መገንባት እጅግ አስፈላጊ ሲሆን የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም ተገነባ የሚባለው ደግሞ መንግሥት የነደፋቸውን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና የልማትና የዴሞክራሲ ዕቅዶችን በብቃትና በጽናት መፈፀም የሚችል እንደ አንድ አካል የሚንቀሳቀስ የለውጥ ሠራዊት ኃይል መፍጠር ሲቻል ነው፡፡ ስለዚህ የምናከናውናቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችንና ግቦችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስፈፀም በተቀናጀ መልክ ሚናቸውን በብቃት መወጣት የሚችሉበት የለውጥና ልማት ቡድን በመገንባት ነው፡፡

የለውጥ ሠራዊት በተቋሙ መገንባት ያስፈለገበት መሠረታዊ ምክንያት የለውጥ ስራዎችን በውጤታማነት ለመፈፀም ያለመ ሲሆን የሚገነባው የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የለውጥ ሠራዊት በአመሰካከቱ፤ በክህሎቱና በአውቀቱ የተሟላና ባስተሳሰብ የተለወጠ በጸረ ድህነት ትግሉ ላይ በግንባር ቀደምነት በመንቀሳቀስ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን በመፈፀም የህዳሴውን ጉዞ እውን ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ ሠራዊት ለመፍጠር ነው፡፡ ለዚህም የለውጥ ሠራዊቱ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በጀመራቸው በድህነት ላይ የሚደረጉ ዘመቻዎችና የስርዓቱ አደጋ በሆነው በኪራይ ሰብሳቢነት ላይ ለሚካፄደው ትግል ድጋፉን ከመስጠት. እና በዘርፉ የተያዘውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን በተደራጀ መንገድ እንዲፈፀም ያስችላል፡፡

ስለዚህም አመራሩንና ሠራተኛውን በከፍተኛ ደረጃ አንቀሳቅሶ ቀጣይነት ያለው የዕቅድ አፈፃፀምና የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ የአመራሩና የሠራተኛው ክህሎት እንዲሻሻል፤ እንዲሁም በየደረጃቫው የሚያጋጥሙትን ማነቆዎች መፍታት እንዲቻል ብቃት ያለው አመራርና ፈፃሚ የመፍጠር ሥራ የመንግሥት ግንባር ቀደም ስራ ነው፡፡

ይህንኑ አውነታ ታሳቢ በማድረግ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በየደረጃ ያሱ አመራርና ፈፃሚ አካላትን በለውጥና ልማት ቡድን በማደራጀት በተለየ ኃላፊነትና ቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ የተለየ ግንባታ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ መመሪያ ተዘጋጀቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ጳጉሜ 05፥2018
የትምህርት ሚኒስቴር
Ministry of Education
ነሀሴ 20፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን-1
Addis Ababa City Public Property Administration Authority