የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ/203/2003 የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት መስረያ ቤት ነው፡፡ ኤጀንሲው ከጡረታ ፈንድ በሚመደብ በጀት እንደሚተዳደር በዚሁ ደንብ አንቀጽ 11 ተመልክቷል፡፡ በዚሁ መሠረት የተቋሙን የአስተዳደር ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ሕግና ግልጽ አሠራር በተከተለ ሁኔታ በስራ ላይ ማዋልና ስራውን ስርዓት ባለው መንገድ መምራት ያስፈልጋል፡፡ መስሪያ ቤቱ ከጡረታ ፈንዱ በሚመደብ ገቢ የሚተዳደር በመሆኑ፤
የራሱ የሆነ የንብረት አስተዳደር ፖሊሲና መመሪያ ሊኖረው እንደሚገባ በውጪ ኦዲት፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባለሙያዎች አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ ከዚሁ አንጻር በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት፣ በሪጅን፣ በቅርንጫፍና በመስክ ጽ/ቤቶች ያለውን ቋሚ ንብረት በአግባቡ መመዝገብና ማስተዳደር እንዲሁም የንብረት አወጋገድን የሚመራበት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ማውጣት አስፈለጊ ሆኖ መገኘቱ ይህ የንብረት አስተዳደር መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡