በኢትዮጵያ ምርት ገበያ መጋዘኖች ከግብይት ፈጻሚዎችና ከአቅራቢዎች ውክልና ተቀብለው የምርት ርክክብ አገልግሎትን በማከናወን ሥራ ላይ የተሠማሩ የመጋዘን ወኪሎች የሚሰጡትን አገልግሎትና ተጠያቂነታቸውን በሕግ በመወሰን አሠራራቸውን በሥርዓት የሚመራ፣ ግልጽ እና ዘመናዊ የግብይት ሥርዓቱን የሚያጠናክር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የኢትዮጵያ ምርት ገ በያ ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 551/1999 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 34 ንዑስ አንቀጽ (2) ሥር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አወጥቷል፡፡