የመመሪያ መለያ: 533/2013
ቀን: ታኅሣሥ 5፥ 2010 ዓ.ም.
Language: Amharic

ግል መገልገያ ዕቃዎች መመሪያ ቁጥር 533/2013

በአየር መንገድም ሆነ በየብስ ከውጭ አገር የሚመጡ መንገደኞች፤ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን እና በተለያዩ ሙያዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ለማገልገል በህጋዊ መንገድ ተቀጥረው የሚመጡ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ወይም የዉጭ አገር ዜጎች፤ መንግሥት በሚያደርገው ልዩ ጥሪ መሠረት የሚመጡ ኢትዮጵያዊያን ወይም ትውልደ አትዮጵያዊያን ወይም የውጭ አገር ዜጎች የሚስገቧቸው እና የሚስወጧቸው እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት ውጭ አገር ቆይተው ጠቅለው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያስገቧቸውን ለንግድ የማይውሉ የግል መገልገያ እቃዎች የቀረጥና ታክስ ኣከፋፈል በሚመለከት ወጥ የሆነ አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

ለንግድ የማይውሉ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ቀረጥና ታክስ አወሳሰን በሚመለከት ወጥ የሆነ የታሪፍ መጣኔ ስርዓት ተፈጻሚ እንደሚሆን በጉምሩክ አዋጁ የተደነገገ በመሆኑ፣ በአየር ትራንስፖርት ለሚጓጓዙ መንገደኞች የሚሰጠዉን የጉምሩክ አገልግሎት ማሰለጥ አስፈላጊ በመሆኑ፣

የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እንቀፅ 224 ፣2 (52) እና 39(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የገንዘብ ሚኒስቴር

Ministry of Finance

Similar Directives

ጳጉሜ 05፥2018
የትምህርት ሚኒስቴር
Ministry of Education
ነሀሴ 20፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን
Addis Ababa City Public Property Administration Authority