የስራ ዕድል ፈጠራና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ በሀገራችን ሆነ በከተማችን ከተጀመረ 1996 ጀምሮ ላለፉት ወዲህ በርካታ ዓመታት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የገቢ አቅም በማሳደግና ድህነትን በማስወገድ ሰፊ ድርሻ እያበረከተ የመጣ ከመሆኑም በተጨማሪ ዘርፉ በራሱ የተፈለፈሉበት ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መሠረት ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት በዘላቂነት ለማረጋገጥና ወደ የሚያስችል ዘርፍ ሆኗል፡፡
ልማታዊ ባለሃብቶች የጣለና አሁን እየተገኘ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በዚህ መሠረትም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መመሪያ በከተማ ደረጃ ተዘጋጅቶና ፀድቆ ወደ ተግባር የተገባና አደረጃጀትና አሠራር በመፍጠር ስራ ፈላጊዎችን በመለየት በመረጡት የሥራ መስክ በህጋዊ መንገድ ከማደራጀት ጀምሮ ለአንቀሳቃሾች የሚሰጡ አገልግሎቶች እና መንግስታዊ ድጋፎች ከአንድ ቦታ እንዲያገኙ የማድረግ እንቅሳቃሴዎች የነበረ ቢሆንም አገልግሎቱ በአንድ ቦታ በተሟላ ሁኔታ ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡
በመሆኑም የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ፣ የትርጉም አረዳድ እና አተገባበር ላይ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ፈጻሚዎች የግንዛቤ ልዩነት የዝግጁነትና የአፈጻጸም ችግር በመኖሩ በሥራ ፈላጊዎችና በኢንተርፕራይዞች ተገቢውን ድጋፍ በሚፈለገው ደረጃ አለመሰጠቱ ተገልጋዮችን ለእንግልት ብሎም ለተስፋ መቁረጥ እየዳረገ በመሆኑ በዘርፉ ዕድገት ላይ ችግር ሆኖ ይገኛል፡፡