የመመሪያ መለያ: 769/2013
ቀን: የካቲት 19፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የዕፅዋት አዳቃይ መብት ረቂቅ መመሪያ ቁጥር 769/2013 የዝግጅት ሂደት፣ ማብራርያ እና አስፈላጊነት

የዕፅዋት አዳቃይ መብት ከአዕምሮአዊ ንብረት መብት እንደ አንደ የሚቆጠር ሲሆን፤ የዚህ መብት ጥበቃ በተመሳሳይ ከኢኮኖሚያዊ ልማት ጋር ትስስር ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ የዕፅዋት አዳቃይ መብት በምርታማነት ዕድገት ላይ የራሱ የሆነ አስተዋፅዖ አለው፡፡

ይህን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማስገኘት ሲባል አዳዲስ ዝርያዎችን ከውጭ የማስገባት አስፈላጊነት በቅድሚያ የሚነሳ ጉዲይ ሲሆን ዝርያውን ያፈለቁ አዳቃዮች ከግኝታቸው ተጠቃሚ ማድረግ ባለመብቱን እና በዘርፉ የተሰማሩትን አዳዲስ ግኝቶች ከማነሳሳት ባለፈ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በምግብ ራስን ለመቻል ከፍተኛ ጥረት ለሚያደርጉ ሀገራት የሚያስገኘው ጥቅም የጎላ ነው፡፡

በተጨማሪም ከዚህ አዋጅ በፊት የነበረው የዕፅዋት አዳቃዮች መብት አዋጅ ቁጥር 481/1998 ከነዐባሪውና ከዓለም ዓቀፍ አሠራር እና ሁኔታዎች ካለመጣጣሙም በላይ የማስፈፀሚያ ደንብና መመሪያ ሳይወጣለት በመቅረቱ ሥራ ላይ ሳይውል በአዋጅ ቁጥር 1068/2010 እንዲተካ ተደርጓል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የግብርና ሚኒስቴር

Ministry of Agriculture

Similar Directives

ጳጉሜ 05፥2018
የትምህርት ሚኒስቴር
Ministry of Education
ነሀሴ 20፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን-1
Addis Ababa City Public Property Administration Authority