የመመሪያ መለያ: 668/2013
ቀን: ነሐሴ 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

ዓመታዊ የተሽከርካሪዎች ደኅንነት የቴክኒክ ምርመራ አገልግሎትአሰጣጥን ለመቆጣጠር የወጣ መመሪያ ቁጥር 668/2013

የሀገሪቱን የትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጐት በማሟላት ረገድ መከናወን የሚገባው ፈርጀ- ብዙ ተግባር የመኖሩን ያህል በአገልግሎት አሰጣጡም በኩል አሁን ያለውን የተሽከርካሪ አቅርቦት በብቃትና በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል በዘርፉ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት የመስጠት አስፈላጊነቱ የጐላ ነው፡፡ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነትን በማረጋገጥ በኩል የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣንና በየደረጃው ያሉ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ መ/ቤቶች እንዲሁም የክልል እና የከተማ መስተዳድር ትራንስፖርት ቢሮዎች ለዘርፉ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በጋራ እየሰሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ከእነዚህ ተግባራዊ ጥረቶች መካከል የተሽከርካሪዎችን የቴክኒክ ደኅንነት በማረጋገጥ ረገድ በስፋት እየተስተዋለ ያለውን የትራፊክ አደጋን የመቀነስና ህብረተሰቡም ደኅንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ በኩል ባለፉት ዓመታት የተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የቴክኒክ ብቃት ምርመራ ሥራ ለግል ድርጅቶች ተሰጥቶ በተሻለ ብቃት እና በዘመናዊ መሣሪያ ተደግፎ መከናወን ያለበት በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት አግኝቶ ባለሀብቶች ውክልና ወስደው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ጉድለት ምክንያት የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ከመቀነስም ሆነ የተገልጋዩን ህብረተሰብ ምቾትና ደኅንነት ከማረጋገጥ አንፃር የተሻለ ለውጥ ማምጣት አልተቻለም፡፡ ለዚህም እንደ ዋነኛ ምክንቶች ከሚወሰዱት ውስጥ ውክልና የወሰዱ የምርመራ ተቋማት ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የወጣውን ስታንዳርድ ጠብቀው አለመሥራት፣ ውክልና ሰጪው አካል የሚያደርገው የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ማነስ፣ የምርመራ \ ተቋማትን ለማደራጀት፣ ለመደገፍ፣ ለመከታተልና ለመቆጣጠር የወጣው መመሪያ ቁጥር 04/2004 የነበሩበት የግልፅነት፣ የተጠያቂነትና የትግበራ ውስንነቶች ናቸው፡፡

በመሆኑም እስካሁን የነበረውን ጅምር የሥራ ጥረት በማጠናከር የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ከነበሩ የሥራ ልምዶችና ከሚስተዋሉት አንዳንድ የአሠራር ችግሮች አንፃር የተሟላ ሁኔታ በማመቻቸት የውክልና አሰጣጥና ዓመታዊ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ምርመራ አገልግሎት በተሟላ አደረጃጀት የተደገፈ፣ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ያካተተ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል ባለሥልጣኑአንቀጽ 49/2/ መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

Ministry of Transport and Logistics

Similar Directives

ጳጉሜ 05፥2018
የትምህርት ሚኒስቴር
Ministry of Education
ነሀሴ 20፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን
Addis Ababa City Public Property Administration Authority