የመመሪያ መለያ: 673/2013
ቀን: ሐምሌ 1፥ 2006 ዓ.ም.
Language: Amharic

በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የቁርስ፤ የምሳና የማደሪያ ቦታዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 673/2013

በመላው አገሪቱ የሚሰጠውን መደበኛ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሥርዓት ለመምራትና የተጠቃሚውን ሕዝብ መሠረታዊ የመገልገል መብት የጠበቀና ፍላጐቱን ሊያረካ የሚያስችል የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ለማድረግ ትኩረት የተሰጠው ሥራ ነው።

በአገልግሎት አሰጣጡ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎች ባላቸው የሥራ አቅም ብቃት በደረጃና በቀለም እንዲለዩ ከማድረግ ጀምሮ የትራንስፖርት ተገሰጋዩ በመረጠው ደረጃ መገስገስ እንዲችል ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ከመደረጉም በላይ ሌሎች መሠረታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቶች እንዲሟሉም ቀጣይነት ያለው ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ማመሳሰሻ ተሸከርካሪዎች እየተሰጠ ካስው አገልግሎት አኳያ ከሃገሪቱ መዲና በመነሳት ወደ ተሰያዩ የክልል ከተሞች በሚያደርጉት የጉዞ ስምሪት የኅብረተሰቡን የመንቀሳቀስ ፍላጐት በማሟላት በኩል ተገቢ ግስጋሎት እየሰጡ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከሚሰጠው አገልግሎት ጎን ለጎንም የጉዞ መስመሮችን የመንገዶች ሁኔታና በአገልገሎት አሰጣጡ ለተገልጋዩ ሕዝብ ሲሟሉ ከሚገባቸው በጉዞ ወቅት ከአንድ መነሻ ቦታ እስከ መድረሻ ቦታ በሚደረግ ጉዞ የሚኖረውን የጊዜ አጠቃቀም አሰልቺነት እንዳይኖረው ከማድረግ ባሻገር ተገልጋዩ ሊያገኝ የሚገባውን የቁርስና የምሳ እንዲሁም የማደሪያ ቦታ ሰጥትው በአግባቡ እንዲተገበር ለማድረግ ሲባል ይህንኑ የሚያሟላ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ለተፈጻሚነቱ መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡

በመሆኑም የሚሰጠውን መደበኛ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከመንገደኞች የጉዞ ምቹነትና ተገልጋዩ በጉዞ ወቅት ሊሟላለት ከሚገባው የቁርስ ፤ የምሣና የማደሪያ ቦታ አገልግሎት አኳያ የባስሥልጣኑ መሥሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 468/97 በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት እንደተገለጸው በመንገዶች ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች የሥራ አቅምና ደረጃ እንዲሁም የዘርፉን አሠራር ማሻሻስ የሚያስችል አዳዲስ አሰራሮችን ለዘርፉ እድገት አማራጭ ስልቶችን ማመቻቸት› በሚል አግባብ አገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላስሻ የትራንስፖርት አገልገሎት ላይ የተሰማሩ ኦፕሬተሮች የሚተገብሩትን ይህን መመሪያ አዘጋጅቶ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

Ministry of Transport and Logistics

Similar Directives

ጳጉሜ 05፥2018
የትምህርት ሚኒስቴር
Ministry of Education
ነሀሴ 20፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን-1
Addis Ababa City Public Property Administration Authority