የንግድ ምልክት ወኪልነት አገልግሎት ብቃት ላይ የተመሰረተ በታማኝነትና በታታሪነት የሚሰራ ስራ በመሆኑ፣ የንግድ ምልክት ወኪሎች ብቃት ደረጃ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር የተመጣጠነ እንዲሆንና የተገልጋዩን ፍላጎት በሚያረካ የእውቀት ብቃት ላይ መመስረት ስላለበት የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ የሚኒስትሮች ደንብ ቁጥር 273/2005 አንቀጽ 51 ለዕ/ቤቱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የንግድ ምልክት ወኪሎች የብቃት የምዘና፣ ምዝገባና አሠራር ሥርዓት መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል፡፡