ተቋሙ የተሰጠውን ተልኮ በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ሰው ኃይል ልማት ቀዲሚውን ሥፍራ የሚይዝ በመሆኑ፣ ለዚህ ወሳኝ ተግባር አስፈላጊ ከሆኑ ስልቶች መካከል አንድ እና ዋነኛው የሠራተኛ የመፈጸም አቅምን በሥልጠና ማሳደግ መሆኑን በመረዳት፣
የሥልጠና አፈጻጸም በሕግ ማዕቀፍ በአግባቡ ከተመራ ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገ ውን ጥረት ከዳር ለማድረስ አይነተኛ መገልገያ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደረር ገቢዎች ቢሮ በሰራተኞች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 99/2010 አንቀጽ 18(4) መሠረት ይህን የሥልጠና አፈፃፀም መመሪያ አውጥቷል፡ ፡