የይቅርታ እና ምሕረት ቦርድ ጽ/ቤት በሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሥር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን የይቅርታ እና ምሕረት ጥያቄዎችን የማስተናገድ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ይቅርታን በሚመለከት ጽ/ቤቱ የሚከተሉት ተግባራት እና ሃላፊነቶች አሉት፤ የይቅርታ ማመልከቻዎችን መቀበል፤ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማሰባሰብ፤ ለቦርዱ ለውሳኔ ማቅረብ፤ የቦርዱን መዛግብትና ሰነዶች፤ ውሳኔ የተሰጠባቸውን፤ በፕሬዝዳንት የፀደቁ ውሳኔዎችን በአግባቡ መያዝ ፤መጠበቅ፤ ስታትስቲክስ ማዘጋጀት፤ ይህንንም ውሳኔ ይቅርታ ጠያቂው ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት በማሳወቅ አፈፃፀሙን መከታተል፤ የይቅርታ ምስክር ወረቀትም መስጠት፣ ስለይቅርታ ውሳኔ ዋጋ ማጣትና የቅጣት ፍርድ አፈፃፀም መቀጠል በቦርዱ የሚሰጠውን ትእዛዝ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንዲሁም ከይቅርታ ጉዳዮች ጋር ተዛማችነት ያላቸውን ሌሎች ሥራዎች የሚያከናውን ሲሆን ምሕረትን በሚመለከት ጽ/ቤቱ ለቦርዱ አባላት አስተዳደራዊ አገልግሎት መስጠ፣ የቦርዱን መዛግብት፣ ሰነዶችና ውሳኔ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች በአግባቡ መያዝ፣ መጠበቅ፣ የስብሰባ ጥሪ ለቦርዱ አባላት ማስተላለፍ፣ አጃንዳዎችንና አስፈላጊ ሰነዶችን ማሰራጨት፣ በተጨማሪም ለቦርዱ ሥራ ስኬታማነት የሚረዱ ሌሎች ተግባራቶችን ያከናውናል፡፡