የግዥ ስራ አስፈጻሚ በሀብት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ስር የሚገኝ የስራ ክፍል ሲሆን፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግዥዎችን ማለትም የአገልግሎት፣ የግንባታ፣ የምክር እና የዕቃ ግዥዎች እንዲሟሉ ያደርጋል። የስራ ክፍሉ የግዥ አገልግሎቱን ለመፈጸም በመንግሥት የወጡ አዋጅ፣ መመሪያዎች እና የአሠራር ማንዋሎችን በመከተል የሚከናወን ይሆናል። በተለይ የስራ ክፍሉ የሚያከናወናቸውን ተግባራት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሲሆን፣ የእያንዳንዱን የስራ ክፍል ፍላጎቶች በማሰባሰብ እና በማደራጀት ለአፈጻጸም በተዘጋጀውና በጸደቀው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ ያደርጋል። በተቋሙ የሚፈለገው የዕቃ እና የአገልግሎት ዓይነት ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን በማረጋገጥ ስራውን በማከናወን ወቅታዊ ሪፖርት ለሚመለከተው እንዲደርስ ያደርጋል።

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ብርሃኑ አስፋው ጫካ

ስራ አስፈፃሚ