የፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ በሃብት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን፤ በሥራ ክፍሉ የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች፡-
- ለተቋሙ የተፈቀደዉን በጀት በፋይናንስ አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ መሠረት የቀረቡ የሂሳብ ሰነዶች በማጣራት ክፍያ መፈፀም፤
- የደመዉዝ፣ የመደበኛ እና የካፒታል በጀት ሥራ ማሰኬጃ የገንዘብ ሚኒስቴር በአሰቀመጠዉ ፕሮግራም መሠረት የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት በማስረጃ በማስደገፍ መጠየቅ፤
- በፋይናንስ አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ መሠረት የቀረቡ ሂሳብ ሰነዶች በማጣራት ክፍያ መፈፀም፤
- በየዕለቱ የመደበኛ፣ የካፒታል እና በተቋሙ የተለያዩ የፕሮጀክት ሂሣቦች የአገልግሎትና የአቅርቦት ክፍያዎች በIFMS የሂሣብና በጀት ሞጁል የምዝገባ ሥራ ማከናዎን፤
- በመሥሪ ቤቱ ሥም የተከፈቱትን የባንክ ሂሣቦች ወጪ ገቢያቸዉን ክትትል በማድረግ ከሂሣብ መዝገቡ ጋር የባንክ ማስታረቂያ መሠረት፤
- ለተቋሙ የተመደበዉን በጀት ከወጪ ጋር በማገናዘብና ክትትል በማድርግ የበጀት ዝዉዉር እና በማሰረጃ በማስደገፍ ተጨማሪ በጀት መጠየቅ፤
- በሁሉም የሂሣብና ባንክ መዝገቦች የተመዘገቡትን በወሩ የተለያዩ የሂሣብ ሪፖርቶች ለሚመለከታቸዉ ለዉጪና ለዉስጥ የሥራ ክፍሎች በማዘጋጀት ማቅረብ፤
- የመደበኛና የፕሮጀክት የሂሣብና ባንክ መዝገቦች የሂሣብ ሠነዶች እንደባህሪያቸዉ ለወስጥ ኦዲት፣ ለዋዉ ኦዲትር አና ለዉጪ ኦዲተሮች ለሂሣብ ምርመራ ሥራ ማዘጋጀት፤ ለክፍላችን ከተሰጡት ኃላፊነቶቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
