የመሠረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ በሃብት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን በዚህ የስራ ክፍል በተቋሙ የሚገዙና እና በስጦታ የሚገቡ ንብረቶችን ማሰራጨት ማስተዳደርና የመቆጣጠር ስራዎችን፣አጠቃላይ የተቋሙ ተሽከርካሪዎችን ምደባ፣ ስምሪት መስጠት ፣የሰርቪስ ጥገና እና ስራዎችን ማከናወን እንዲሁም የመቆጣጠር ስራን እንዲሁም በጠቅላላ አገልግሎት ቡድን በኩል በዋና መስሪያ ቤት እና 11 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የቢሮ መገልገያ እቃዎችን ብልሽት ሲያጋጥማቸው የጥገና ስራ ፣የመብራት ፣የውሃ ፣ስልክ ብልሽት ሲያጋጥም ጥገናዎችን እና ክፍያዎች ክትትል ማድረግን ተቋሙ ባስገባቸው ሕንጻዎች ላይ የተገጠሙ የሊፍት ፣ጀነሬተሮች ሰርቪስ እና ጥገና እንዲደረጉ እና የጉዳይ አስፈጻሚ ስራዎችን የሚከወኑበት እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚያከናወናቸው ዋና ዋና ስራዎች ከግብ እንዲመቱ ከሚያስችሉ የስራ ክፍሎች አንዱ ሲሆን የስራ ክፍሉ ከተሰጡት ኃላፊነቶቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
