የሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት

የሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት በፍትሕ ሚኒስቴር ሥር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6/13 መሠረት በዐቃቤያነ ሕግ የሚሰጡ ዉሳኔዎች በሕግ መሠረት መከናወናቸውን ለማረጋገጥ፣ ጉድለቶትን በጥናት አስደግፎ በመለየት እንዲታረሙ ማድረግ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና መልካም ተሞክሮዎች ለማስፋት የተደራጀ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡ ለዚህ ተልእኮ መሳካትም የመስክ፣ የዴስክና ድንገተኛ የሕግ ኦዲት በማከናወን የግኝቶችን ምክረሃሳብ ወይም የውሳኔ ሃሳብ ለሚኒስትር ወይም ግብረ መልስ ለሥራ ክፍሎች ማቅረብ ከተጣሉበት ኃላፊነቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ልኡል ካሕሳይ ወልዱ

ዳይሬክተር